VISITORS COUNTER


VISITORS COUNTER

Ticker

6/recent/ticker-posts

ትዝ ይልሃል ?


 

ያ መንደር ግን ትዝ ይልሃል ካፋፉ ላይ የቆምንበት

ከዳገቱ ከፍ ብለን ቁልቁለቱን የሳቅንበት

ልቤ እዛጋ ትቶኝ ቀርቷል ከውድ ነብሴ ተነጥሎ

ቅጠሉ ላይ ፈልግልኝ ቀርቶ እንዳይሆን ተንጠልጥሎ

ደሞ እንደውም ካስታወስከው ቡና ታዞ ስንጠብቅ

ከመምጣቱ ባንተ ማንኪያ ከኔ ሲኒ ስትጠልቅ

እዛህ ቦታ ተከታይህ ቀልቤ ትቶኝ ላንት ዘምቷል

ካገኘኸው ባክህ አስማማኝ  ከኔ ርቆ ሰነባብቷል

ልትቀር ስትል መነጫነጭ ጎሸም ጎሸ ደርሶ ነካ

ተወት ተወት ስታደርገኝ በስህተቴ እጥፍ ስለካ

ቦርሳው ከእጄ ሲንሸራተት በጎን ነገር ያየህበት

ካስታወስከው ነብሴ ታሟል የዛን እለት

በናፍቆትህ እየከነፍኩ እሱን ትቼው በሳምንቱ

ደስታዬን እዛው ቀበርኩ ላንተም ላይሆን ያው በከንቱ

ስፈልግህ ይሰማኛል ዛሬ ደግሞ ግራሩ ስር ተቀምጬ

ከስቃዬ ስገላገል በብህር ጫፍ እንዲህ አም

                          በሜሮን መለሰ ሀብተወልድ  

Post a Comment

1 Comments