ከወንበሮቹ በአንዱ ከአንዱም ጥግ ላይ ነጠል ብሎ የተቀምጠው ላይ ናት፡፡ ከወንበሮቹ በአንዱ ከአንዱም ልክ እንደ
ምስሶ ከቤቱ ማህል ላይ የተቀመጠውን ጠረጴዛ ከከበቡት ወንበሮች በአንዱ ላይ ነው፡፡ እኔ ታዛቢዋ ከበረንዳው ወንበሮች በአንዱ ላይ
ጀርባዬን ለመንገዱ ሰጥቼ ከጓደኞቼ ጋር ለመመሳሰል ያዘዝኩትን ጣዕም
አልባ ሎሚ በሻይ ፉት እያልኩ ካፌው በታጠረበት መስታወት ወደውስጥ
ሁኔታቸውን እከታተላለሁ፡፡ እውነት ለመናገር ከሁለቱ ሰዎች ውጪ ሌሎች ጠረቤዛዎች ላይ ሰዎች አሉ፡፡
አይኖቼ ግን ሁለቱን ሰዎች
ሰረቅ አድርገው ሲተያዩ እጅ ከፍንጅ ያዛቸው፡፡ መተያየታቸው እኮ ላይገርም ይችላል እሺ ምን አስገነገጣቸው ? እሺ መደንገጣቸው
ይሁን የልጅቷ ሽኩርምሚት የበዛበት ፈገግታ እንኳንስ ብቻውን ቴብል
ሞልቶ የተቀመጠን ሸበላ ቀርቶ የኔንም ቀልብ ስቦታል፡፡ አይኖቿን ሰበር አንገቷን ዘመም አድርጋ ስልኳን መነካካት ጀመረች፡፡ እሱስ
መች በዚህ ሊያቆም ጭራሽ በስልኩ አድፍጦ ጥርሶቹ ባልተገለጡበት ፈገግታ ቀና ማለቷን በግንባሩ እያየ ይጠባበቃል፡፡ ደግሞ እንዴት ያለ አመቺ ቦታ ላይ እንደተቀመጠኩ፡፡
እያንዳንዷ እንቅስቃሴያቸው ከእይታዬ አያመልጥም ፡፡ ትንሽ ቀና እንደማለት ብላ
ጨርፋ አየችው እመኚ አይሽዋል ደግሞ ቀናያልሽው እራሱ እሱን ለማየት ነው ብላት ደስ ባለኝ ነበር እሷ ሆዬ አንተን ለማየት አይደለም
አይነት ዙሪያዋን ቃኝታ አላስፈላጊ መኮሳተር ገበረች፡፡ ሳይታወቀኝ ፈገግ ስል
“…..አይደል ?” አለኝ በስተቀኜ የተቀመጠው ጓደኛዬ
ሁሌ ለነሱ መሃል ላይ ተቀምጦ መመስከር ስልች ብሎኛል፡፡ በዛ ላይ የኔ ምስክርነት ምንም ቢሆን በሚያወሩት እርህስ ላይ ለውጥ እንደማያመጣ
አሳምሬ ስለማውቅ ያሉትን ሳልሰማ እራሴን በአዎንታ ነቀነቅኩላቸው፡፡
“እኮ…” ሲል ሰምቸዋለው ነገር ግን ቀጥሎ የተባባሉትን ከመስማት የሚበልጥ ትህይንት በሸበላው ተደረገ እጆቹን የመንጠራራት ያህል
ዘርግቶ አስተናጋጅ በምልክት ጠራ ፡፡ ደበረኝ እውነት ደበረኝ ምናለበት
ግን ትንሽ ቢቆይ መች እኔ ብቻ እሷም ድንገት ፊቷ ወደቀባት እና ተጋፍጣ ታየው ጀመር፡፡ አቤት መሯሯጥ ደግሞ የአስተኛጋጇ ፍጥነት
….. ጭራሽ ተጠጋችው ….እርፍ ጭራሽ መሳሳቅ ምን ብሏት ይሆን ? ብዬ ሳልጨርስ ጎንበስ አለች በጆሮዋ ወደ ልጅቷ እያየ የሆነ
ነገረ አላት፡፡ ኦኦኦ ኢሄ ሰው ጨዋታ ያውቃል ፡፡ ወደ እሷ እያየ
እንደሆነ ስታውቅ በወንበሯ ላይ ተደላድላ የመጀመሪያውን አይነት ፈገግታ ለገሰች፡፡ ውስጤ በሳቅ እና መሽኮርመም ሲሞላ ተሰማኝ፡፡
አፍረት በመፈላለግ እየተሸነፈ እየመጣ ነው፡፡
አስተናጋጇ በፈገግታ በመጣችበት ቅልጥፍና ባዶ ያደረገውን የማኪያቶ ሲኒ ይዛ ተመለሰች፡፡
እሱም ፊት ለፊት አነጣጥሮ ለሽኩርምሚታም ፈገግታዋ በሚስቁ አይኖቹ
ጭንቅላቱን ግራ እና ቀኝ በመጠኑ…. በመጠኑም ሳይሆን በጣም በትንሹ ምናልባትም ለሌላ ሰው በማይገባ መልኩ አነቃንቆ አይደልልልልል….አይነት
ነገር ብሏታል፡፡ እውነት ብሏታል በደንብ አይቼዋለሁ አፍረት ነጥብ እየጣለ ነው፡፡ ጎላ ያሉ አይኖቿን በዝግታ ከድና ገለጠቻቸው፡፡
እየተባባሰ……ነጣ ያለ እጅጌ ጉርድ ሸሚዙን ኮሊታ በሁለት እጁ አስተካክሎ ወደስልኩ ሲያጎነብስ ቀረፃ ላይ ናቸው እንዴ ብዬ ለቅፅበት
አሰብኩ፡፡ መቼም ኢሄን ያክል እረጅም ሲን ከት ሳይባል አይቀጥሉም፡፡ ሸበላው ግን እዚህ ጋር ቀሽም ሆነ ልጅቷን ከሙድ አወጣት
እኔንም አበሳጨኝ፡፡ ቆጣ ብላ በእጇ የፅሁፍ ምልክት እሱ ለጠራት አስተናጋጅ አሳየቻት፡፡ እባክሽ ትንሽ ተረጋጊ እንጂ ልጅት በጣም
እያስታወቀብሽ እኮ ነው ደግነቱ አስተናጋጇ ጭንቅላቷን በፈገግታ ነቅንቃ እሺታዋን ገልፃ ወደ ሌላ ጥሪዋ ሄደች፡፡
ተይ እንጂ አይነት
ነገር አላት በአይኑ ፈርጣማ እጆቹ የሞሉት እጅጌ ውስጥ ጣቶቹን ለመክተት እያታገለ በእግረ መንገድም የራሱን እጅ ለዘብ አርጎ እያሻሸ፡፡
እሺ አሁን አንገቷን ሰገግ አድርጋ አይኖቿን አጥብባ ማየቱን ምን አመጣው፡፡ እሰይ የኔ ቀብራራ እሱስ የፈለገው ኢሄንኑ አይደል
ወደኋላው ለጠጥ ብሎ ጥርሶቹን አሳያት እኔ ለዚህስ ቃልም የለኝ፡፡ አስተናጋጇ አንድ ቁራጭ ቴራሚሶ ኬክ ከብዙ ፈገግታ ጋር ጠረጴዛዋ
ላይ አስቀምጣላት ወደሸበላው እያየች በጆሮዋ አውርታት ሄደች፡፡ እዚህ ጋር ነገር ተቀየረ አቤት ሹካ አያያዝ አቤት ኬክ አቆራረስ አቤት አስተያየት አቤት አጎራረስ፡፡ አነጀሊና ጁሊ ምን
ትተውናለች ደግሞ ሁኔታዋ ሁሉ ጨዋነት የሞላበት መሆኑስ አይኖቿ ከሱ ላይ ሳይነቀሉ ማድረግ መቻሏስ፡፡
ጅንኑ እንደዛው ዘና ብሎ
እንደተደገፈ እያያት አንድ ሰው ከየት መጣ ሳልለው መጥቶ ያካለበው ጀመር አስተናጋጇም እንደተማከረ ሰው ከላባው ሁለቱ ተፈላላጊዎች መሃል እንደቆመ ሳይቀመጥ ቢሉን ይዛለት መጣች ገንዘብ አስቀምጠው በጥድፊያ እየወጡ ዞር ብሎ አያት እሷም
ስታየው የሁለቱም ደስታ ከሽፎ እንደነበር እኔ ምስክር ነኝ ፡፡ አላስችል ያለኝ እኔ ግን በአጠገቤ ሲያልፍ “እና በቃ….?” አልኩት ፊቴን ወደሱ አዙሬ…..ታዛቢ እንደነበረበት ሲረዳ
በአፍረት አጎንብሶ እየሳቀ የፍጥነት እርምጃውን ቀጠለ፡፡ ሰው እንዴት
በቅፅበት ሙሉ ህይወት ይኖራል ተያዩ ፣ ተፈቃቀዱ ፣ ተገባበዙ፣ ተናደደች እሱም አባበላት ፣ ልሂድ ስትል አባብሎ አስቀራት፡፡ በቅፅበጽ
ያለምንም ቃላት የዘመናትን እድሜ ሲኖሩ ቆይተው በመሃላቸው ጣልቃ የገባው ከላባ ለያያቸው እኔ ደግሞ ነገር አለሙን እረስቼ እነሱን
ሳኗኑር መቆየቴ ፡፡ እንግዲህ ደግሞ ያገናኛቹህ እንጂ ሌላ ምን ይባላል፡፡
በደራሲ እና ጋዜጠኛ ሜሮን መለሰ ሀብተወልድ
10 Comments
Wow amazing yehone yene jagena 🥰🥰
ReplyDeleteበጣም አመሰግናለሁ
Deleteሁሌም ጻፊልን!
ReplyDeleteእስከዛሬ የት ተደብቀሽ ነውስ?!
በጣም አመሰግናለሁ
Deleteከዚህ ወዲያ አብረን እንዘልቃለን
Nice article..wedjewalew..gn አንድ ወጥ ከሚሆን some line break binorew wubet alew...anyways u r the best keep it up
ReplyDeletebetam amesegnalew am ready to gone fix it
DeleteTnx for applying my comment fixing the content
ReplyDeletei really appreciate your concern please keeping touch
DeleteTitle: A Glance, A Gesture, A Moment – Reflecting on Meron Melese’s Café Narrative
ReplyDeleteAuthor: Someone
Date: July 9, 2025
Category: Reflections, Ethiopian Literature, Creative Nonfiction
---
📝 Post Content:
A Glance, A Gesture, A Moment – A Reflection on the Subtleties of Urban Connection
Sometimes, a café isn’t just a place for coffee—it’s a quiet stage where human emotions are performed in real-time. In her delicately woven narrative, journalist and author Meron Melese Habtewold draws us into one such moment: a slow-burning social interaction that unravels quietly yet powerfully between two strangers—and the observant narrator—at a typical Ethiopian café.
What stands out is not what is said, but rather what remains unsaid.
Meron’s prose is filled with cinematic details: the tension in a turned neck, the awkward beauty of a flirtatious misstep, the cold sting of a smile misunderstood. A woman fidgets with her phone, a man reacts too late, the air between them thick with interpretations. The narrator watches silently, a stand-in for all of us who sit in cafes, watching life unfold across tables we do not dare approach.
> "Not all closeness is connection," the piece seems to whisper.
"And not all gestures carry the truth they appear to offer."
This story captures the loneliness that coexists with presence, and how we often find ourselves witnessing life rather than participating in it. We see people laugh, connect, hesitate, pretend, and drift—each behavior shaped not just by desire but also by doubt, social rhythm, and emotional muscle memory.
It’s a mirror to the urban experience: people surrounded by others, yet quietly negotiating invisible lines of intimacy, pride, and vulnerability.
As a reader, I walked away not just entertained but introspective. It made me ask:
How often am I a silent witness to real stories unfolding around me?
What performances have I staged myself in the name of self-preservation or pride?
This piece is proof that the most meaningful stories aren’t always in dramatic events, but in the delicate choreography of everyday life.
---
🔖 Tags:
#MeronMelese #EthiopianLiterature #CreativeNonfiction #AmharicProse #UrbanLife #CaféStories #HumanConnection #Reflection
what an amazing expression it is ? i really really really respect your concern and i appreciate your deep interpretation please keeping touch. Thank you so much🙏
ReplyDelete