VISITORS COUNTER


VISITORS COUNTER

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለምን ነበር ???

  


 

አንዴ ደውሎ እንገናኝ ካለ እንደማያቆም ስለማውቅ እንጂ ስደርስ ምንም የረባ ነገር እንደማያወራኝ አሳምሬ እያወቅኩ ነው የሄድኩት፡፡ በእርግጥ እሱ አልችልም እያለ ለምኜ እያገኘሁ እስኪሰለቸው ስለዛህ …. አለ አይደል በቃ ስለሱ ያወራሁለት ቀን ተቆጥሮም አያልቅ፡፡ ግን ዛሬ ላገኘው አላሰኘንም ነበር፡፡ ስደርስ በደስታ ተሞልቶ አቀባበል አገረገልኝ፡፡ መቼም በመሀላችን ህግ የለም። ነገር ከመሃሉ ነው የሚጀመረው  ተቀምጬ ትንሽ እንደቆየሁ 

“የማንዋደድ ነው የምንመስለው፡፡ ምክንያቱም ሰዎች መዋደድ ብለው ባወጣው መስፈርት ስንለካ እንኳንስ ለተመልካች ለራሴም እውነት እንደሚሉት እየመሰለኝ ይሆን እንዴ/ ብዬ እጠራጠራለሁ ግን እኮ ልቤን የማውቀው እኔ ነኝ፡፡ ብላ ፅፋ ማስታወሻ ደብተሯን ከድናው አቀማመጧን ለመተያየት እንዲመቻት እራቅ አደረገችው፡፡” ሲያወራልኝ አተራረኩ ያለ ፍላጎቴም አጊኝቼው ቢሆን ምስል ይከስትልኛል ግን የሆነ የማለቋቋመው አይነት ደባሪ አጨራረስ አለው

“ስትፅፍ እኔ እንዳነበው ስታስብ እንድረዳት ስታወራ እንድሰማት ትፈልጋለች፡፡ እኔስ ምን ገዶኝ አይን ከማይት አይጠግብም ጆሮም ከመስማት አይሞላም ብሎ የለ ቅዱስ መፅሐፉ፡፡ ስታወራ እያየሁ ነው የምሰማት፡፡ ነገሯ ኁሉ ግልፅ ነው ስታወራ ከፊቷ ጀምሮ ሁሉ እንቅስቃሴዋ ልቤን ይማርከዋል እየመለስኩ እንድወዳት ያደርገኛል፡፡ ግን መውድድ ላንቺ ምንድነው?” አለኝ፡፡ ልክ እንደ ጀማሪ ፈላስፋ አይኑን እያጠበበ ነገር ለማተለቅ ሲጣጣር አንተም ሆንክ ጓደኝነት ገደል ይግባ በይው ያሰኘኛል፡፡

“ይሔን ልትጠይቀኝ ነው እንዲ አጣድፈህ የጠራኸኝ?” ለሰከንዱ ስንት አይነት ስሜት እንዳስተናገድኩ ሴጣን በኔ ላይ ድግሱን ሊያበላ እነቂው እነቂው፡፡ የእስከዛሬ ንዴትሽን ልኩ ድረስ ነግረሺው ይውጣልሽ፡፡ ግን ምን ክፉ አነጋገረሽ ፊት ለፊቱ የተቀመጠውን ጠርሙስ አንስተሸ …….በስመ አብ ብዬ የጠላትን ድብቅ ሴራ አፍርሼ፡፡ ሳፈጥበት

“አረ ለዚህ አይደለም እውነት ለዚህ አይደለም” ብሎ አበረደኝ ልክ አልባ ንዴት ማሳየት ሳበዛ እየታወቀኝ ነው ግን ማወቅ ጥቅም የማይሰጥበት ወቅት ላይ ነኝ፡፡ ደግሞ እኮ እንዴት ያለውን ከበርቴ ስንቱን በብሩ የሚያሾረውን ሰው እንደሆነ ጓደኝነት በሚል ተልካሻ ሰበብ በንዴቴ እንዲህ የማሸብራ:: “ተረጋጊ እንጂ” አለኝ

“ተረጋግቻለሁ ፡፡ እሺ ለምንድነው አቻኩለህ የፈለከኝ?”

“ስላስቸኮልኩሽ ይቅርታ  ከተገናኘን ስለቆየን ነው ግን ለዚህ ስለ እሷ ላወራሽ አይደለም የፈለኩሽ” የማውራት ጉጉቱ ሲጠፋበት ታየኝ ፡፡ ተፀፀትኩ

“እሺ እና  ምን አለችህ?” አልኩት በንጭንጭ

“ምነው ከሰውዬሽ ጋር ሰላም አይደላችሁም እንዴ ምንድነው የሚያነጫንጭሽ?” አለኝ።  ምን አለበት ግን እንዳወራ ባይቆሰቁሰኝ

“አንተስ ምን አልካተ?” ልክ እንዳልሰማ ሰው ካድ !!!!

“ብዙ ነው ያወራችልኝ ደስ እያለኝ ሰማዋት። ከልቧ አወራችልኝ ። እናህም እሷ ሰዎች የሚሉትን ሳትል አታወራም ትክክለኛውን ነገር ብታውቀውም ግን የሚያሳስባት ትክክል መስላ መታየቷ ነው እንደምወዳት ታውቃለች እንደምትወደኝ አውቃለሁ ይሔንን አምና እንደመኖር የምትጨነቀው የምንዋደድ መስለን ስለመታየታችን ነው”

“እስካሁን የነገርከኝን እኮ ከዚህ በፊት በተለያየ መልክ ነግረኸኛል……ይልቅስ ልንገርህ ባለፈው ድንገት ከሰዎች ጋር መጥቶ ነበር……………………..” 15 ደቂቃ ታግሶ ሰምቶኝ ….”ባለፈው ያልኩሽ ስራ እኮ ተሳካልኝ›› አለኝ በመሀል

“በእውነት……እንኳን ደስ አለህ…….እናልህ በጣም አናዶኝ ስለነበር ሲደውል ዝም አልኩት እሱ ብቻ መሰለህ”………….25ደቂቃ፡፡ ሰምቶኝ

“ግን አንቺ እንዳሰብሽው ባይሆንስ?” አለኝ ሳቁን እያፈነ… “በኋላ ላይማ ……………”ተጨማሪ 20 ደቂቃዎችን አውርቼ ስጨርስ አስፈላጊ የስራ ስልክ ተደውሎለት ተሰነባብተን ተለያየን፡፡ ማታ ወደመኝታዬ ሳመራ ስለሷ ለማውራት አይደለም አጣድፌ የጠራሁሽ ካለኝ  ቆይ ታዲያ ለምን ነበር ??? የሚል ጥያቄ ተሞላው  

 

 በሜሮን መለሰ ሀብተወልድ

 

 

Post a Comment

6 Comments

  1. ይህንን የፃፉትን እጆች የጥበብ አምላክ ይባርካቸው

    ReplyDelete
    Replies
    1. አሜን 🙏 ኢሄንን የመረቀውንም ቅን ልብ ፈጣሪ ከክፉ ነገር እና ከሀዘን ይጠብቅልኝ

      Delete