VISITORS COUNTER


VISITORS COUNTER

Ticker

6/recent/ticker-posts

በቀጠለ ህይወት ውስጥ

 





ለምሳሌ በድሮ ጊዜ ኤሌትሪክም ሆነ መብራት አልነበረም፡፡ ልክ እውቀቱ ሲኖራቸው አሁን በምንጠቀምበት መንገድ ህይወታችንን አቅልለውልናል ግን ደግሞ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ በኤሌትሪክ ምክንያት ብዙ ጉዳት የደረሰባቸው እና የሞቱም ለቁጥር የሚበዙ ሰዎች አሉ እሺ ታዲያ ኤሌትሪክ በእግዚያብሔር ወይስ በሴጣናዊ ሃይል ነው የተገኘው ?”

“እኔ ካሉት ጋር የማይገናኝ ምሳሌ ነው የሰጠሽው”

“እሺ እማዬ በቀጥታ ላገናኝልሽ መሰውሩን የሚጠቀሙት መኖራቸው ትውልድን የሚያጠፉ፣ ሊሰረቁ የሚችሉትን፣ ጠላት ደግመው እንዳይገኙ ሊያጠፋቸው የሚፈልጋቸውን ቅርሶች ከዚህም አልፈሽ በጠላቶቹ እየታደነ ላለ ሰው ከሆነ ምን ክፋት አለው? ግን ደግሞ መሰውሩን ተጠቅሞ እየዘረፈ ወይም እያጭበረበረ ላለ ሰው ከሆነ መጥፎ ይሆናል፡፡ የትኛውም እውቀት በራሱ መርዛማ አይደለም አጠቃቀማችን ነው መድሐኒትም መርዝም የሚያረገው!” 

“በጣም ጥሩ ትናገሪያለሽ የኔ ቅመም ግን የማይጠቅም እውቀት ሸክም ነው ሲሉ አልሰማሻቸውም እኛ በለመድነው የህይወት ድግግሞሻችን ውስጥ በሰላም ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ብንኖር ይሻለናል….”

Post a Comment

0 Comments