ወንድም አለም የእናቴ ልጅ በአንድ ክንድ የታቀፍን
ልጅነቴን የተጋራህ ክፉ ደጉን ያሳለፍን
እህትህ ያን ዋርካ መሰልኩ መጥፎም ጥሩም በኔ አለፈ
ሃዘን እድሜው እጅግ አጥሮ ውስጤ በደስታ ከነፈ
ልቤ በቦታዋ ቦረቀች ዘለለች እንደ እንቦሳ
ነብሴ መንሳፈፍ ተመኘች እንደ ሸማ ፍቅር ለብሳ
እናማ ምኑን ልንገርህ በየቱስ ቃላት ገልጬ
በደስታ እቅፍ ውስጥ ወደኩ ከሃዘን ጉያ አምልጬ
የጨፈንኩ እንደው ላፍታ ምስሉ ከአይኔ በር ታትሟል
ከስጋት ተላቅቄያለሁ ልቤም በፍቅሩ አምኗል
እራቅኩ ካየኸኝ ስፍራ መናኝ መናኝ አደረገኝ
ትንሽ ሰንበትነት ብሎዋል መማረኩም ከማከኝ

0 Comments