ቅኔ ቅኔ ይለኛል ዝረፊ ዝረፊ
የማይጣስ ድንበር በሚስጥር እለፊ
የወዳጄ ወዳጅ ወዳጄም አይደለ ?
ቀልድ እነግርሻለሁ ውስጤ እህህ እያለ
ቀልዱ በቅኔ ነው ቅኔው ደሞ ስውር
በሳቅሽ ሲስቅ ሳይ ይቀልልኝ እንደው የህመሜ ክምር
እንዲህ ካልወጣልኝ ዝም እንዳልል ነገር ጥቃቱ ያመኛል
እንዳልናገረው ደሞ እንዳላሰከፋሽ ሀዘን ያስፈራኛል
እኔ ማምለጫ የለኝ ምርኮኛሽ ማርኮኛል
ሲከፋሽ ሲከፋው እኔን ይከፋኛል
አረ ምን በወጣሽ አንቺ ምትከፊ
ደስታሽ ሲበዛ ነው በቤታችን ደጃፍ አስሬ ምታፊ
ቅኔ ቅኔ ይለኛል ዝረፊ ዝረፊ
ዝግ ባለ ድምፅሽ የማይጣስ ድንበር በእንጉርጉሮ እለፊ
እስቲ ልገላልፅሽ ልቤን ደስ እንዲለው
ባንቺ አይደለም እንዴ በመምጣት መቅረትሽ የቤቴ ምሰሶ ጠበቅ ላላሚለው
አይገባሽም እንጂ ወድጄሽ አይደለም የምሸነግልሽ
ልቤ ሌላ እያለ ባፌምደልልሽ
አንቺ ማለት ለኔ የቤቴን ገፅታ ድንገት የለወጠ እርግማን ይዘሻል
በህይወቴ ገብተሽ የደስታ እና ሃዘኔ ምክንያት ሆነሻል
ልክ የክፋት ንግስት ሆነሽ ይታየኛል ደግነት ማታውቂ
ሰውን ካለውዴታ አስጨንቀሽ ይዘሽ ማታነቃንቂ
ሀዘንሽ መጥፎ ነው በቀጥታም ባይሆን ለኔም ሰማኛል
ጥላቻን ታቅፌም ሳቅሽ ያስቀኛል
የወዳጄ ወዳጅ ወዳጄም አይደለ ?
ቀልድ እነግርሻለሁ ውስጤ እህህ እያለ
ቀልዱ በቅኔ ነው ቅኔው ደግሞ ስውር
በሳቅሽ ሲስቅ ሳይ ይቀልኝ እንደው የህመሜ ክምር
0 Comments