VISITORS COUNTER


VISITORS COUNTER

Ticker

6/recent/ticker-posts

እንዴት ሊሆን ቻለ ?

 

 


አደይ ጠዋት ተነስታ ከእናቷ ጋር ቁርስ እየበሉ ስለ አባቷ ሲያነሱ

“እማዬ……. አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ?” አለች

“ምንድነው?”

“ማታ ደህና እደሪ ብዬሽ መኝታ ቤቴ ስገባ አይተሺኛል ?”

“ቀድመሺኝ ስለወጣሽ ስትገቢ አላየውሽም፡፡ ወደላይ ስትወጪ ግን አይቼሻለው”

“እሺ ከትላንት ወዲያስ?”

“አይቼሻለው” አሉ ባያስታውሱትም ወደ ነጥቧ እንድትገባ

“እያየሺኝ ገብቼ ከውስጥ በሩን ስቆልፈው ሰምተሽ በነጋታው ጠዋት በሩ ከውስጥ እንደተቆለፈ እኔ ግን ውስጥ ባልኖርስ?”

“ሊሆን አይችልም! ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም! ወደፊትም አይፈጠርም! እንደዚህ አይነት ቅዠትሽን እንድታቆሚ ሺህ ጊዜ ነግሬሻለው ብትሰሚኝ ጥሩ ነው !”

“ለምን ትቆጫለሽ እማዬ ጥያቄ እኮ ነው……”

“እንደዚህ አይነት ጥያቄ አትጠይቂኝ”

“ለምን?”

“ሊሆን ስለማይችል ነዋ” አሉ በቁጣ

“ጥያቄ እኮ ነው የጠየኩሽ”

“እንግዲህ ተናገርኩ” ብለው ተነስተው ሊሄዱ ሲሉ

“እኔ ግን ሊሆን ስለመቻሉ ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ ለምን መሰለሽ እዚሁ ቤት እዚያኛው ክፍል ውስጥ ገብቶ ሲቆልፍ ያየሁት አባቴ ሲጠፋ በአይኔ አይቻለሁ” ብላ ወደ ፀሎት ቤቱ አሳየቻቸው

“አሃ…. እንግዲህ አዋራ ሆኖ ይሆን?” አሉ በንዴት ጦፈው

“የእኔም ጥያቄ እሱ እኮ ነው እማ፡፡ እንዴት ሊሆን ቻለ?”

“እማ አትበይኝ!”

“እሺ በቃ የኔ ውድ እናት በእኔ ምክንያት ቀንሽን በብስጭት አትጀምሪ የዚያን ነገር ምንነት ለማረጋገጥ ማረግ የምችለውን ሁሉ አርጌ እውነቱ ጋር እደርሳለሁ”

“እኔ አርፈሽ ህይወትሽን እንድትቀጥዪ ነግሬሻለሁ እንደዚህ ካሰብሽልኝ የምልሽን ስሚኝ”

“እወድሻለሁ እናቴ በቃ ቻው” ብላ በአየር ላይ ስማቸው ወጣች

አሁን አሁን አደይ አለመግባባት መፍጠር በራሱ ሰልችቷታል፡፡ በተለይ ከእናቷ ጋር ክርር ያለ አለመግባባት ላለመፍጠር ከመጨቃጨቅ ይልቅ ቀስ በቀስ ስለ አባቷ የምታስበውን ነገር ግጭት በማይፈጥር መልኩ በመጠቆም ወ/ሮ አዳነች ነገሩን እንዲያስቡት ለማረግ እየጣረች ነበር፡፡ ምንም እንኳን እያለች ያለችውን ነገር ለመቀበል ባይፈልጉም ጠቁማቸው የምታልፈውን ነገር ሳያሰላስሉት አይቀሩም፡፡

 

                                     ከመፅሐፉ የተወሰደ

Post a Comment

0 Comments