“ለአሁን ሳሮን ስላለች የሚስት ያለህ ማለቱን ማቆም እመርጣለሁ፡፡ በፕሌን ስትሄድ ከደመና በላይ ሆነህ ደመናውን እና ከደመናው ስር ያለውን መሬት አይተኸው ታውቃለህ ሳሚ? በደመናው ምክንያት መሬት ላይ የሚፈጠረውን ጥላ ፣ ሰፋፊ ሜዳዎች ፣ ተራሮች እና ብዙ ነገሮች ማየት ይቻላል፡፡ ግን ከደመና በላይ ያለው መንገድ ብቻ ነው፡፡ የኛ ህይወት የተመሰረተው ከደመና በታች ባለው በዚህ መሬት ላይ ነው፡፡ ከላይ ሆነህ እንድታይ የሚያረግህ ፕሌን እንኳን ፕሌን የሚሆነው መሬት ላይ ነው ከምንረግጠው መሬት ስር ደግሞ ወርቅ እና የከበሩ ማህድናት አሉ እኛ በሁለቱ መሃል ነን ፡፡ ከሁሉም በላይ የሚገርመኝን ነገር ልንገርህ …..ከፍ ካለ ደመና በላይ ሆነህ ወደመሬት ስታይ እይታህ በደመናው ይጋረዳል ደመና ባይኖር እንኳ ከርቀቱ የተነሳ የምታየውን ነገር ምንነቱን ለመለየት ትቸገራለህ፡፡ የዚህ ጊዜ በሰማያት አለ ብለን የምናምነውን አምላክ ረቂቅ ሃይል እረዳለሁ፡፡ ምክንያቱም ከሰማያት ሆኖም ከደመና በታች ያለነውን ሁላችንንም ለይቶ ያውቀናል፡፡ ስለዚህ በአምላክህ ሃያልነት እንድታምን ያረግሃል” አለ ኮስተር ብሎ
ታዲዮስ “ይሴ…….የዛሬው ለየት ያለ ነው እውነት” አለ በግርምት አይቶት፡፡ በዝምታ ጥቂት እንደቆዩም እርስ በእራሳቸው ተያይተው እኩል
“ከደመና በታች ……ሃሃሃሃሃሃሃ” ብለው ተሳሳቁ
ከመፅሐፉ የተወሰደ

0 Comments