የአደይ እናት ወ/ሮ አዳነች የአክስታቸው ልጅ ልጇን ትድር ስለነበር ሠርግ ተጠርተው ክፍለ ሃገር ወደ ምትገኘው የአክስታቸው ልጅ ቤት ሀሙስ ማለዳ የሄዱት በሶዶ ጉራጌ(ሶዶ ክስታኔ) ማህበረሰብ ተወላጆች ዘንድ በደማቅ ሁኔታ የሚከበረው የእንሾሽላ ስርዓት ላይ ለመገኘት እና እስከ መልስ ቆይተው እሮብ ወደቤታቸው ሊመለሱ ነበር፡፡
ሠርጉ ቅዳሜም ቢሆን እሁድ የእንሾሽላ ስርዓት የሚደረገው አርብ ማታ ሲሆን፤ ጠላ በእንስራ ተሞልቶ ከድፎ ዳቦ ጋር ይቀርብ እና ከበሮ እየተመታ “እንሾሽላ ያግድልችጎይ ያቦ አዮ ቤለ” እየተባለ ሙሽሪት ወይም ሙሽራው በጋብቻ የሚቀላቀሉት ቤተሰብ የማን ዘር ነሽ(ነህ) ከተባልሽ(ከተባለክ) የእከሌ ዘር ነኝ በይ(በል) እየተባለ፡፡ ከሚያኮራ ዘር መገኘታቸው የሚገለፅበት እና የዘር ሃረግ እየተዘረዘረ የሚወደስበት ከሠርግ ጋር የተያያዘ ባህላዊ ስርዓት ነው፡፡ እዚህ የአያት፣ የቅድመአያት፣ የአክስት እና የአጎት እንዲሁም በእናትም በአባትም በኩል የሚዛመዱ በአካል እንኳ ለመተያየት ሞት ጊዜ ያልሰጣቸውን ዘመዶች ስም ከተሰበሰበው ሰው ጭብጨባ እና ድምፁ ጎላ ብሎ እንዲሰማ ፀሃይ ሲንቃቃ ከሚከርመው የከበሮ ድምፅ ጋር ሙዚቃውን እየተቀባበሉ እያወጡ ሲያወድሱ መስማት ቋንቋውን ለማይረዳው ሰው እራሱ አንዳች ውርር የሚያረግ ስሜት አለው፡፡
👆 ከመፅሐፉ የተወሰደ👆
1 Comments
የእሕቴ ልጅ በዚው ስርአት ነው የተዳረችው
ReplyDelete