VISITORS COUNTER


VISITORS COUNTER

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከትምህርት ጋር ፀብ


 

“አምሳል አንቺስ ትምህርቱን ተትሽው ልትቀሪ ነው እንዴ ምነ እያሰብሽ ነው?” አሉ መልሷን በጉጉት እየጠበቁ

“ውይ የኔውስ አይነሳ ጋሽዬዋ መልሼ ድርሽም አልል”

“እንዴ ለምን አምሳል ?” አለ ታዲዬስ በመለሷ ተገርሞ

“ተትምህርቱ ጋር ምናችንም አልገጠመም እንደው የተረፈኝ በመመላለስ መኳተን ብቻ ነው፡፡ ቲያወሩት ቢገባኝም እውቀቱ አልዘልቀኝ አለ ክፍሉ ቲጨምርማ ይብስም ተራርቀነው አረፍን”

“ሃሃሃሃሃሃ……ይቅርታ አምሳልዬ የሳቅኩት በአንቺ ሳይሆን በአገላለፅሽ ነው፡፡ እያወራሽ ያለሽው እኮ ስለታጨሽለት ሰው እንጂ ስለትምህርት አይመስልም….ሃሃሃሃሃ” አለ ይስሐቅ፡፡ አምሳልን ጨምሮ ሁሉም አብረውተት ሲሲቁ ጠቂት እንደቆዩ

አደይ “እኔ ማወቅ የምፈለገው የከበደሽ ምኑ እንደሆነ ነው ማለቴ ያልገባሽን እና ችግር የሆነብሽን ነገር ነው” አለች በቅንነት ልትረዳት አስባ

“አይ አደይዋ እሱን ባውቀው ተደጁ አያድርሰኝ እል ነበር? ምኑ እንደ ማይገባኝም እንኳ አለተረዳሁትም እውቀቱ አልዘለቀኝም ቢገባኝም እረሳዋለሁ ለሱ አለተፈጠርኩም በቃ ለማንበብ እና ለመጣፍ ካልቸገረኝ ይበቃኛል ኢሄስ ያለዘለቀው ስንት አለ አይደል” አለች በኩራት በድጋሚ ሳቃቸውን ሲያበቁ ሳምሶን

“ሃሃሃሃሃሃ…….እኔ እራሱ አሁን የአምሳል አነጋገር ልክ እንደ ይሴ ነው የተሰማኝ…… አንቺ በጣም ብልህ ነሽ እንዳልተረዳሽው ማወቅሽ እራሱ ትልቅ እውቀት ነው፡፡ አሁን እኮ ፈተና እየሆነብን ያለው ያልገባንን ነገር እንደገባው ለመሆን የምናረገው ትግል ነው፡፡ ገጠር እያለሽ አልታቻጨሽም ነበር ?” አለ ሳምሶን ከይስሐቅ ንግግር ተነስቶ

“ታጭቻለው” አለች አምሳል አንገቷን ደፍታ

ወ/ሮ አዳነች “በደንብ ንገሪን እንጂ አምሳልዬ በስንት አመትሽ ታጨሽ ሰውዬውስ የት ደረሰ?”

“በ7 አመቴ ነው የታጨሁ አበዬ ምትወስዳት ተ9 አመቷ ኋላ ነው ሁለቱን አመት ፊደል ትቁጠር ብሎ አስጠንቅቆት ስለነበር ቤቴ ቆየሁ” ብላ ንግግሯን ስታቋርጥ ይስሐቅ

“ከዛስ ተዳርሽ ….?” አለ በጉጉት

“ትምህርቱ ይገባኝ መስሎኝ ብማር ነው የሚሻል ታልያ አንዱ ገደል እገባለው እያልኩ ታስቸግር እንዳያገኘኝ እናቴ እደጋማው ስፍራ ያሉት ዘመዶቿ ቤት ሰደደችኝ ኋላም እናነት ጋር መጣሁ”

“ሰውዬው ስትጠፊ ቤተሰቦችሽን አልረበሸም?” አሉ ወ/ሮ አዳነች፡፡ ታዲዮስም ቀጠል አርጎ “የስንት አመት ሰው ይሆናል?” አለ

“እሱማ የት ይቀራል ብለው ነው እትል አበዬ ካሳ ከፈለው እና በሽምግልና ጨረሱ …..የዛኔ የ30 አመት ሰው ይሆናል ሌላ አግብቶ ፈቶ ነበር እኔን ያጨው በስተመጨረሻ ከእሱም ተትምህርቱም ነጣ ወጣው፡፡ አሁን የተበላበትን ተጠረቤዛው ላይ ላነሳሳ እና የጋሽዬን ልጅ ስራ ላግዛት” ብላ ከተቀመጠችበት ስትነሳ ሌላ ጥያቄ እንዳይመጣባት ለማምለጥ የተናገረችበት መንገድ ሁሉንም ከልብ አሳቃቸው

Post a Comment

2 Comments

  1. በርቺ እጅግ ወድጄዋለሁ መፅሀፍሽን

    ReplyDelete
    Replies
    1. በጣም አመሰግናለሁ

      Delete