.....ተሰናብታ እየሄደች ለራሷ“በመኖር ከማውቀው ነገር እና ትምህርት ቤት ተመላልሼ ካገኘሁት እውቀት ውጪ በዚህች በምኖርባት ሀገር እንኳን ምን እንዳለ እና ችግር እንዴት እንደሚፈታ እንኳን አልተማርኩም… በሀገሬ ያለውን ከገራገርነት፣ ከማረስ እና ከብቶች እያገደ ከማርባት ሌላ እውቀት ያለው ከማይመስለኝ ከገጠሩ ማህበረሰብ ሲጣሉ በሽምግልና እርቅ፣ ሲታመሙ ቅጠል፣ በግፍ ሲሞቱ ወይም ጠፍተው ሲቀሩ ነብስን ጠርቶ ማናገር፣ ሲጠየቁ ወንጌል ጠቅሶ መመለስ፣ ሲራቡ ተካፍሎ መብላት፣ የሰውን ሸክም የመጋራት ልምድ፣ ላሎለዱት ልጅ እንደ ወላጅ መንሰፍሰፍ፣ ሳይዋለዱ ቤተሰብ ሆኖ በወዳጅነት የመኖር ባህል፡፡ አባቴ በሌለበት ጊዜ በቀጠለ ህይወቴ በነዚህ ድንቅ ነገሮች መሃል እየኖርኩ እንደሆነ እንኳን ያስተዋልኩት አሁን ነው” አለች.........
ከመፅሐፉ የተወሰደ

1 Comments
Endet.band.war.wust.yehn.yahl.view.aganyash
ReplyDelete