እናቷ ዛሬ ባይናገሯት ኖሮ መሸነፏን ላለማመን እያረገች የነበረው ጥረት ከንቱ እንደቀረ አታስብም ነበር፡፡ አልጋዋ ላይ ትራሷን አቅፋ ቁጭ ብላ ፊት ለፊቷ አልጋው ላይ የተቀመጠውን ስልክ እያየች ልክ እንደሰው ታወራለት ጀመር፡፡ “በጣም መጥፎ ሰው ነው፡፡ እኔ ለእሱ ጥሩ ስሜት በሌለኝ ጊዜ እንኳን ሲደውል እያነሳው ሳናግረው እና ሳገኘው አልነበር? ወይስ ስንቀራረብ እሱ ሲያስበኝ ከኖረው አንሼ ታየውት?” ድምፁዋ እየሻከረ እና እንባ እየተናነቃት “በዚያች አጭር ደቂቃ ውስጥ በአንዴ ብዙ ጥያቄ ነው የጠየቀኝ፡፡ የቱን ምን ብዬ መመለስ እንዳለብኝ የማስብበት ጊዜ ሊሰጠኝ አይገባም? እኔ እኮ አባቴን በማጣት የተጎዳው ሰው ነኝ፡፡ ሌላ ሰው ለማጣትም ሆነ ከእሱ ጋር በዚህ ሁኔታ ተቀራርቦ ለመራራቅ ዝግጁ አልነበርኩም” ብላ በረጅሙ ተንፍሳ እንባዋን እየጠራረገች “ወይ አደይ ገረመው ….ይኼኔ እኮ እሱ በሰላም ተኝቷል እኔስ? ….እኔ ምን እያረኩ ነው?” ብላ በድጋሚ የወረደ እንባዋን ጠራርጋ አልጋዋ ውስጥ ገብታ ተኝታም ያለማቋረጥ የሚወርድ እንባዋን ከስር ከስር እየጠረገች ፈገግ ብላ “ለምንድነው በረሃ ላይ ብቻውን እንደተጣለ ሰው የማውቃቸው ሰዎች ሁሉ እየናፈቁኝ እና ብቻውን እንደቀረ ሰው እየተሰማኝ ያለው” ብላ በአቶ እንቁ ፈገግ ብለው በቀሩ አይኖቻቸው መታየት እና ምንም ሳይናገሩም ሳይንቀሳቀሱም ፍቅር በሚሰጡበት መንገድ ይኼ መጥፎ ስሜት እንደሚቀላት ስለምታውቅ ሲነጋ አቶ እንቁ ጋር ለመሄድ ወስና ተኛች፡፡
ከመፅሐፉ የተወሰደ
1 Comments
Amazing 😉 😉
ReplyDelete