VISITORS COUNTER


VISITORS COUNTER

Ticker

6/recent/ticker-posts

ባስፈልግህ ሀገር ካገር


                                

ባስፈልግህ ሀገር ካገር ባሳስስህ በከተማ

የውሃ ሽታ ሆነህ የት ተገኝተህ አንተማ 

 

ባገኝህ ማባበያ ቃላት ስለቃቅም

አንተን ማሞገሻ ቅኔ ሳጠራቅም

 

ውዴ ብዬ ፣ፍቅሬ ብዬ ፣ማሬ ብዬ

የኔ ብዬ ስጦታዬ አንባ መጠጊያዬ

 

መሽቶ ነጋ ስፈልግህ ዘመን አልፎ ዘመን መጣ

ላንተ ስቀኝ ለሌለኸው ጥቁሩ ፀጉሬም እንደው ነጣ ፡፡



Post a Comment

0 Comments