“አንተ ግን አለህ?”
“አይ የለሁም ….ሰማይ ቤት የደወልሽ መሰለሽ እንዴ?”
“የምትለው አታጣም ….ምን ሆነህ ጠፋህ?”
“እስክፈለግ እየጠበኩ ነዋ አዲቲ ”
“እሱስ ልክ ነህ ስትፈለግ ትገኛለህ ስልኩንም ሊጠራ ሲል ነው ያነሳኸው”
“ባነሳ ችግር ባላነሳ ችግር እንደው የት ልድረስ?”
“በል አትማረርብኝ ….እንዴት ነህ?”
“አለው ከደመና በታች እየኖርኩ ምን እሆናለው ብለሽ ነው አንቺ እንዴት ነሽ?”
“ይመስገን ሰላም ነኝ እኔ እኮ የሚገርመኝ እኛ ፀሐይ ሲያነደን እየዋለ ከደመና በታች የምትለው ነገር ነው”
“ለማስገረምም ከረዳኝ አንድ ነገር ነው ቤት ሰላም ናቸው?”
“ክብሩ ይስፋ”
“ምነው ሰባኪ ሰባኪ ሆንሽሳ የቀረሽ ነጠላ ማጣፋት ነው የነጠላውን ነገር በኔ ጣይው”
“ደግሞ እግዚያብሔርን አላመስግን እንዴ?”
“አረ ተይ ከማይነካኩት አታነካኪኝ እንጂ ምን በደልኩሽ?”
“ሃሃሃሃሃ…… ምን አዲስ ነገር አለ?”
“ባክሽ ላገኝ አልቻልኩም እንጂ ሚስት እየፈለኩ ነው”
“እንዴ እጅማ እንዳትሰጥ በደንብ ፈልግ የቀረህ ባትሪ ነው እሱን በእኔ ጣለው”
“ሃሃሃሃሃ….አገኘሺኝ”
“ፈልጌ መች አጣሃለው ይሴ …ሃሃሃሃ”
“በይ በይ አትጠበቢብኝ በቃ ቻው”
“በእናትህ እንዳትዘጋው ቆይ”
“እሺ ምንድነው ወይስ ናፍቆቴ አሎጣልሽም?”
“እምምም….እንደዛህ ነገር”
“ባምንሽ ደስ ይለኝ ነበር “
“ቆይ በእናትህ ትንሽ አውራኝ ቤት እየደረስኩ ነው ማሚ ሰላም ናት?”
“ደህና ናት …እኔ የምልሽ አዲ ዙሩ ደረሰብኝ እንዴ?”
“የምኑ ዙር?”
“ያ አታላቹ ያቀመሳችሁኝ ፅዋ ነዋ…”
“አይ ገና ነው በ3 ሳምንት ተብሏል ሳሚ ጋር ነው”
“አስታውሺኝ በእናትሽ ሚስት ካላገኘው እመጣለሁ”
“እኛ ባጣ ቆዪኝ ነን?”
“እናንተ የትም አትሄዱብኝማ ሚስቴን ግን ቶሎ ፈልጌ ካላገኘዋት አንዱ ከውካዋ ያገባት እና ቆሜ እቀራለው”
“አረ ተው ይሴ እኛ ላንተ ወንበር ለመግዛት አንሰን ነው ቆመህ የምትቀረው?”
“አንቺ ምን አለብሽ እናቴ ለማግባት ስትወስኚ ከፈላጊዎችሽ አንዱን ሱፍ ማልበስ ነው የሚጠበቅብሽ እኔ ነኝ እንጂ ከርታታው”
“ሃሃሃሃሃ…..ህይወት እኮ እንዳንተ አወራር ቢቀል ገነት የመግባት ጉጉታችን ይቀንስ ነበር”
“አሁን ግን ለምን አትተይኝም?”
“አትነጫነጭ ልተውህ ትንሽ እኮ ነው የቀረኝ”
“አምሳል ግን ለምን ዘመዷን አትድርልኝም?”
“ሃሃሃሃሃ ምን ችግር አለ እነግራታለኋ”
“እስቲ ይኼን ቁም ነገር ስሪ”
“ቁም ነገር ይወራል እንጂ አይሰራም እኮ”
“ጀመረሽ ደግሞ ልትጠበቢብኝ ነው፡፡ እውነት አዲ በጣም ነው የምወድሽ ከዚህ በላይ ካወራሁሽ ወሬ ይቸግረኛል”
“አረ ጠላትህ ይቸግረው ሰሞኑን እንገናኛለን” ብላው ተሰነባብተው ስልኩን ዘጉት፡፡ ቤት ስትደርስ የእናቱዋ ተወዳጅ ጨዋታ ተቀበላት ለመተኛት ስትገባ ደግሞ የአሮን ስልክ ከዚያ ደግሞ እንቅልፍ ከታዲዮስ ጋር ያወሩትን መልሳ ላለማሰብ ያረገችው ጥረት በስኬት አበቃ፡፡
0 Comments