VISITORS COUNTER


VISITORS COUNTER

Ticker

6/recent/ticker-posts

Yemabired sir'at / የማብረድ ስርዓት


የማብረድ ስርዓትም ልክ እንደ እንሾሽላ ሁሉ በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ከ እንሾሽላ በተቃራኒ ለሃዘን የሚደረግ ሲሆን በብሄሩ ተወላጆች ሴራ በመባል ይጠራል፡፡ ሴራ ማለት በጉራጊኛ ስርዓት እንደ ማለት ነው፡፡ ታዲያ ማብረድ የሚባለው ሴራ  አንድ ሰው ሲሞት በተቀበረ 12ኛ ቀን ምሳ ይዘጋጅ እና ድፎ ዳቦ ተጋግሮ፣ ንፍሮ ተቀቅሎ፣ ቡና ተፈልቶ ቤተዘመድ ይሰባሰባል፡፡ የማብረድ ስርዓቱን ለማከናወን ሠርዶ በመባል የሚታወቀው የሳር ዝርያ፣ ቂቤ እና ወተት ከተዘጋጀ በኋላ የቤተዘመዱ ትልቅ ሰው ሃዘን ከቤቱ ይውጣ፣ መጥፎ ነገር በመልካም ይተካ እያለ እየመረቀ ሰርዶውን ወተቱ ውስጥ እየነከረ ከቤቱ በራፍ ወደ ደጅ  ይረጨዋል፡፡ በመቀጠልም ቤት ውስጥ የተሠበሠበው ሰው ሁሉ ከተዘጋጀው ቂቤ እና ወተት በማሪያም ጣት( በትንሹዋ ጣት ) ግንባሩ መሃል ላይ ያስነካል በመቀጠልም 3 ወይም 7 ሰው ሃዘን እንዲያበቃ፣ በደስታ ተመልሠው እንዲሠባሠቡ፣ ያዘነ እንዲፅናና፣ ሃዘን ደግሞ በዘር እንዳይመጣ፣ ሀገር ሠላም እንዲሆን ይመርቁ እና ስርዓቱ ኬር ተብሎ ይጠናቀቃል፡፡ የማብረድ ሴራ በማህበረሰቡ ተወላጆች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጥበት ምክንያት ሀዘንን ካላበረድን እና ፈጣሪን የወደድከውን አርገሃል የቀረውን ባርክልን ብለን የፈጣሪን ፈቃድ ካልተቀበልን ሀዘን ይደጋግማል ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡

                                                                      ከመፅሐፉ የተወሰደ

Post a Comment

2 Comments

  1. ይህን መፅሃፍ እየሰሰትኩ በ3ቀን ጨረስኩት ያውም መብራት ስለሌለ በሻማ ነው ያነበብኩት. ደራሲዋን አለማድነቅ ንፉግነት ነው

    ReplyDelete
    Replies
    1. ከልብ አመሰግናለሁ 🙏🏼

      Delete