“ዋናው ባለ ድብርት አንተ ስለሆንክ እንኳን ተዝናናህ፡፡ የሚያሳዝነኝ ሚስት እንኳን ሳላገኝ መመለሴ ነው” አለ ይስሐቅ በቁጭት
ሳምሶን በጣም ስቆ “ ሚስቶች እኮ የሚርቁህ ሚስት እንኳን እያልካቸው ነው” አለና ቀጠል አርጎ “ሚስት እንኳ ይላል እንዴ ጭማሪ አደረጋቸው እኮ” አለ
“አሃ…. አንተ አግብተህ ሦስት የወለድከው እንደዋና ስለምታያቸው ነዋ?”
“እሱንም ስፈልግ አረገዋለሁ!”
“ጫማ መሰለህ እንዴ ስትፈልግ የምታረገው? የፈለካቸው ጊዜ እነሱም ይጠፋሉ የማወራው እኮ ስለፍቅረኛ ሳይሆን ስለሚስት ነው” አለ ይስሐቅ
ታዲዮስ ጣልቃ ገብቶ “ፍቅረኛ ሳትሆን እንዴት ሚስት ትሆናለች?” አለ
“እሱ እንደፈጣሪ አሰጣጥ ነው”
አደይ “እንዴት?”አለች
“አያቶቻችን ፍቅረኛ ተብላ የተሰጠቻቸውን የከንፈር ወዳጅ ትተው ሚስት ተብላ የተሰጠቻቸውን የማያቋትን ቤተሰብ ያጨላቸውን ሲያገቡ እንደኖሩት፡፡ ሚስት ተብላ ስትሰጥ ሚስት ትሆናለች ፍቅረኛ ተብላ ስትሰጥ ፍቅረኛ ከመሆን ሳትሻገር ትቀራለች”
አደይ “ እንዴት እንዴት ነው የሚያፈላስፍህ ታውቆሃል ግን?” አለች
“እኛማ እናወራለን ሰሚ ጠፋ እንጂ” ብሎ ሲስቅ ሁሉም አብረውት ስቀው እንዳበቁ
ታዲዮስ “የእኔ ጥያቄ ሚስት ተብላ የተሰጠችውን ፍቅረኛ ተብላ ከተሰጠችው በምን እንለያታለን የሚለው ነው?”አለ
“እሱን ባውቅ የሚስት ያለ እያልኩ ታገኙኛላቹ ?” አለ በመሰልቸት
ከመፅሐፉ የተወሰደ
0 Comments