#ላሌ ላቡኮ# አንተ ከደቡብ ኦሞ ከካራ መንደር የተገኘህ ጥቁር እንቁ የወንድነት እና የጀግንነት መስፈርት ነህ !!!ከልጆቻቸው ፍቅር የበለጠባቸውን ወግ እና ባህል ተቃውመህ መርጠው ባልሆኑት ነገር እንዲሞቱ የተፈረደባቸውን ህፃናት የታደግክ ጀግና !!!! እኛ ከ ሁለት እና ሦስት ሰዎችጋ እንኩዋ ላለመጋጨት እይምሮዋችን የሚያውቀውን ግፍ እንዳላየ እናልፋለን # ላሌ # እራስህን እና ቤተሰብህን ላደጋ አጋልጠህ ላመንክበት እውነት የቆምክ ..ከባህል ...ከወግ ....እና ከማህበረሰቡ አስተሳሰብጋ የተፋለምክ የጥንካሬ ማሳያ ነህ !!!! በተፈጥሮ ስርዓት የላይኛው ጥርሳቸው ከታች ኛው ቀድሞ በመውጣቱ አልያም በመውለቁ ፤ ከጋብቻ በፊት በመረገዛቸው ሚንጊ በሚል መጠሪያ ተሰይመው በማህበረሰቡ ላይ መከራን ያምጣሉ ተብለው ልክ እንደ እርግማን እየተቆጠሩ ወደ ገደል፣ ወደ ወንዝ እና ዋሻ ተጥለው እንዲሞቱ ማህበረሰቡ የፈረደባቸውን ህፃናት እኔን እንደ ወንዙ እንደ ሸለቆው እና ገደሉ ቆጥራችሁ ልጆቹን ለኔ ስጡኝ የማለት ጥንካሬ ያለህ ብርቱ ሰው!!!!! አንተ የደቡብ ኦሞዋ የካራ መንደር ፀሐይ !!!! የማህበረሰቡን ተፅህኖ ፈርቼ ያላንኩበትን በደል ዝም ባልኩ ጊዜ ሁሉ አንተ ትገዝፍብኛለህ !!!! ሀገሬ እንዳንተ አይነት ሌላውን ለማዳን እራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ጀግናም አፍርታልች!!!!!!! ከሞት ላተረፍካቸው እና ላስተማርካቸው ህፃናት ትምህርት በማይታወቅበት የገጠር መንደር ላነቃሃቸው እና ከጎንህ ለቆሙት ወጣቶች ሁሉ ሞገስ የሆነህ እና የረዳህ እግዚያብሄር ያክብራቹ !!! የሃገሬ ጌጥ ላሌ ላቡኮ የደቡብ ኦሞ ህፃናት ተስፋ ኢትዬጲያዊው ጀግና የኦሞ ቻይልድ መስራች እኮራብሃለው 👏🏾👏🏾👏🏾
#በ ሜሮን መለሰ ሀብተወልድ
0 Comments